Home
About Us
Work Process
Project
News and Events
Gallery
statistical data
Downloads
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 

 

Home Contact Us Vacancy

የመስሪያ ቤቱ አመሰራረትና አደረጃጀት

በ1983 ዓ.ም. በሀገር አቀፍ ደረጃ በተደረገው ሥር-ነቀል ለውጥና በ1985 ዓ.ም. በተደረገው የክልል መንግሥታት ምሥረታ እንዲሁም የነበረው ማዕከላዊ አስተዳደር ተለውጦ ክልሎች ራሣቸውን በራራሣቸው እንዲያስተዳድሩ በመደረጉ በአዋጅ ቁጥር 7/84 መሠረት ቀደም ሲል ከነበረው አደረጃጀት የተፈጥሮ ሃብት የሥራራ ዘርፍ ራራሱን ችሎ በቢሮ ደረጃ የተቋቋመ ሲሆን የግብርና ቢሮም የህብረት ሥራራን፣ የግብርና ግብዓትና ሌሎች ቀሪ የሥራራ ዘርፎችን በመያዝ እንዲቀጥል ተደረገ፡፡ ህዳር 15/88 ዓ.ም የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት የአስፈፃሚ መ/ቤቶችን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን ባወጣው አዋጅ መሠረት ቀደም ሲል ለየብቻ ተደራራጅተው የነበሩት የግብርና፣ የተፈጥሮ ሃብት ልማትና የቡናና ሻይ ልማት ቢሮዎች በአዋጅ ቁጥር 3/88 ተዋህደው የግብርና ቢሮ ተብለው ሲደራራጁ ከነሐሴ 1989 ዓ.ም. ጀምሮ በአዋጅ ቁጥር 14/89 የኅብረት ሥራራ ለብቻው በጽ/ቤት ደረጃ እንዲቋቋም ተደረገ፡፡

የግብርና ቢሮም በአዋጅ የተሰጡትን ሥራራዎች አካትቶ በሁለት መምሪያዎች ተዋቅሮ እስከ 1994 ዓ.ም. ሲንቀሣቀስ የቆየ ቢሆንም በሀገር አቀፍ ደረጃ  ገጠርንና ግብርናን ማዕከል ያደረገ የልማት ፖሊሲንና ስትራራቴጂን በሥራራ ለመተርጎም በሚደረገው ርብርብ የተለያዩ ተቋማትን በቅንጅት መምራራት፣ የሰው ጉልበት፣ ሀብትና ጊዜን በመቆጠብ ቀልጣፋ አሠራራርን መከተል እንዲያስችል ከሞላ ጎደል ተቀራራራራቢና ተደጋጋፊ እንዲሁም ተመሳሳይ የገጠር ልማት ራራዕይ ያላቸውን መ/ቤቶች በአንድ ላይ አስተባብሮ ለመምራራት ሲባል የተደረገውን የአደረጃጀት ለውጥ መሠረት በማድረግና በክልል ተጨባጭ ሁኔታ ላይ በማተኮር በገጠር ልማት ዙሪያ ተግባራራዊ የልማት እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ የሚገኙትን የክልሉ ተቋማት ቢሮዎችንና ጽ/ቤቶችን አቀናጅቶ በመምራራት ቀልጣፋና ፈጣን ዕድገት በማስመዝገብ የገጠሩን ሕዝብ ብሎም አጠቃላይ የክልሉን ሕዝብ ኑሮ ለማሻሻል፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ሁለንተናዊ ዕድገት ለማስመዝገብ የደቡብ ክልል የገጠር ልማት ማስተባበሪያ ቢሮ በ1994 ዓ/ም በአዋጅ ቁጥር 36/1994 ተቋቋመ፡፡

የገጠር ልማት ማስተባበሪያ ቢሮም በሥሩ የግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮን፣ የህብረት ሥራራ ቢሮን፣ የግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩትን፣ የግብርና ግብዓት ባለሥልጣንን፣ የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ጽ/ቤትንና የምግብ ዋስትና ጽ/ቤት በበላይነት ያስተዳደር ነበር፡፡ እዚህ ላይ እነዚህ መ/ቤቶች በተለያየ ጊዜ በተደረገ የአደረጃጀት ለውጥ ሲጣመሩና ለየብቻ ሲደራጁ የቆዩ የተለያዩ የሥራራ ዘርፎች መሆናቸውን እንገነዘባለን፡፡

በቀጣይም ቀደም ሲል በአዋጅ ቁጥር 36/94 ተቋቁሞ የነበረው የመሠረተ ልማት ማስተባበሪያ ቢሮ ሲፈርስ በአዋጅ ቁጥር 66 /95 የመስኖ ባለሥልጣንን፣ የውሃ ቢሮን፣ የገጠር መንገድ ባለሥልጣንና የማዕድንና የገጠር ኢነርጂ ኤጀንሲ በገጠር ልማት ማስተባበሪያ ቢሮ ሥር እንዲተዳደሩ ተደርጓል፡፡ እንደዚሁም በግብርና ሥር ይከናወን የነበረው የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ሥራራ ከተፈጥሮ ሃብት ልማቱ ሥራራ ተነጥሎ በአዋጅ ቁጥር 52/95 የአካባቢ ጥበቃ፣ መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ባለሥልጣን ተብሎ እንዲቋቋምና ተጠሪነቱም ለርዕሰ መስተዳድሩ እንዲሆን ተደረገ፡፡ በተመሣሣይ ሁኔታ የግብርና ግብይትና የብድር ሥራራን ለማጠናከር ሲባል በአዋጅ ቁጥር ...... ከህብረት ሥራራና ከግብርና ወጥተው ለየብቻ የወጪ ምርት ማስፋፊያ ኤጀንሲና የገጠር ፋይናንስ አገልግሎት ፈንድ  አስተዳደር ጽ/ቤት ተብለው ተደራራጁ፡፡ ከእነዚህ መ/ቤቶች መካከል የወጪ ምርት ማስፋፊያ ኤጀንሲ በንግድ ኢንዱንስትሪና ከተማ ልማት ማስተባበሪያ ቢሮ ሥር የነበረ ሲሆን የገጠር ፋይናንስ አገልግሎት ፈንድ አስተዳደር ጽ/ቤት ግን በህብረት ሥራራ ቢሮ ሥር ሆኖ በገጠር ልማት ማስተባበሪያ ቢሮ ይመራራ ነበር፡፡ ነገር ግን አንድ ዓይነት የሥራራ ባህሪ ያላቸውን መ/ቤቶች በአንድነት አቀናጅቶና አስተባብሮ ከመምራራት አንጻር ከ1997 ዓ.ም. መጀመሪያ ጀምሮ የአካባቢ ጥበቃ፣ መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ባለሥልጣንና የወጪ ምርት ማስፋፊያ ኤጀንሲ በገጠር ልማት ማስተባበሪያ ሥር እንዲተዳደሩ ተደረገ፡፡

ይሁን እንጂ ይህ አደረጃጀት የማስተባበር ድርሻውን በተገቢው ሁኔታ ሊወጣና ያለውን የሰው ሃይልና ገንዘብ አቀናጅቶ ለመጠቀም በሚያስችል መልኩ ያልተደራራጀ በመሆኑ ይህን ችግር ለመፍታት በአዋጅ ቁጥር 90/98 የግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ በሚል ስያሜ እንደገና ተቋቋመ፡፡ እንደገና በሚቋቋምበት ጊዜም  ቀደም ሲል በገጠር ልማት ማስተባበሪያ ቢሮ ሥር የነበሩት የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ልማትና የህብረት ሥራራ ቢሮ”፣የግብርና ግብዓትና የአካባቢ ጥበቃና መሬት አስተዳደር ባለሥልጣንን ፣የግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩትን፣የገጠር ፋይናንስ ፈንድ አገልግሎትና የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ጽ/ቤት”'የግብይት ኤጀንሲንና የምግብ ዋስትናና በአንድ ጥላ ሥር በማሰባሰብ በግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ሥር እንዲደራራጁ ተደርጓል፡፡ አደረጃጀቱም የግብርና ልማት፣ የምግብ ዋስትና አደጋ መከላከልና ዝግጁነት፣ የሕብረት ሥራራ ማደራራጃና የግብርና ግብዓት እና የተፈጥሮ ሀብትና ገጠር መሬት አስተዳደር በዘርፍ ደረጃ ሆነው በቀጥታ ለግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ተጠሪ እንዲሆኑ ሲደረግ እንዲሁም የግብይት ኤጀንሲ፣ የግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩትና የገጠር ፋይናንስ አገልግሎት ፈንድ አስተዳደር በጽ/ቤት ደረጃ ተደራራጅተው በቢሮው ሥር እንዲተዳደሩ ተደርጓል፡፡ እንደገናም በግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ በዘርፍ ደረጃ ተዋቅሮ የነበረው የህብረት ሥራራ ማደራራጃና የግብርና ግብዓት ዘርፍ በአዋጅ ቁጥር 106/99 የግብርና ግብዓት ዘርፍና የህብረት ሥራራ ማስፋፊያ ኤጀንሲ በሚል ለየብቻ እንዲደራራጁና ተጠሪነታቸውም በግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ሥር እንዲቀጥሉ ተደርጓል፡፡

Copyright © 2008 South Agricultrue and Rural Development Bureau